በተለይ የክልሉን የመልማት አቅምን መነሻ በማድረግ የምርታማነት ማነቆዎችን ለመፍታ ተግባራትን ለይቶ እየሰራ ያለ ስሆን በሰብል በፍራፍሬ፣ በስራስር ሰብሎች (በእንሰት)፣ በቅመማቅመም፣በቡና ፣ በእንስሳት ምርምር በቦንጋ በግ ፣ በዶሮ፣ በተናዳፊና ተናዳፊ ባልሆኑ ንቦች፣ በእንስሳት መኖ በተፈጥሮ ምርምር በአሲዳማ አፈር፣ በተፈጥሮ ማዳበሪያ፣ በደንና ጥምር እርሻ፣ በአፈርና ዉሃ ጥበቃ ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በመነሻ ዘር ብዘትም በሩዝ፣ ስንዴ፣ ባቀላ፣ ድንች እንድሁም የሙዝ ዘሮችንም እያከባዛ ይገኛል፡፡ የማዕከል አድማሱን ለማስፋት በዳዉሮ ዞን ታርጫ ማዕከል በመክፈት የተመራማሪ ቅጥር በመፈጸም ወደ ተግማር ገብቷል፡፡