• Mon. Dec 23rd, 2024

Southwest Ethiopia Agricultural Research Institute

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

በየተቋማት የሚካሄደው የሰራተኞች ምዘና ውጤታማ እንዲሆን የፈጻሚውን የግል አቅም ማጎልበት ሚናዉ ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፐብሊክና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

Byadmin

Sep 28, 2024
Spread the love

በየተቋማት የሚካሄደው የሰራተኞች ምዘና ውጤታማ እንዲሆን የፈጻሚውን የግል አቅም ማጎልበት ሚናዉ ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፐብሊክና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው ለክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዮትና ለቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል ሰራተኞች በመግንስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ፣ በተቋም ተኮር ሪፎርም እና የስራ አፈጻጸም ምዘና ላይ ስልጠና እየሰጠ ነዉ፡፡

የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት እንደ ክልል የሰራተኞችን የመግንስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ፣ የተቋም ተኮር ሪፎርም እና አፈጻጸም ምዘና ለማሻሻል እየተሰራ ነዉ።

በየተቋማት የሚካሄደው የሰራተኞች ምዘና ውጤታማ እንዲሆን ፈጻሚው የግል አቅም ማጎልበቻ ዕቅድ ከተቋም ጋር በማስተሳሰር በትጋት ሊያከናውን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ዓለሙ በበኩላቸው ስልጠናው ለነገ ተቋማዊ ውጤታማነታችን አጋዥ በመሆኑ ሰራተኞች በአግባቡ ስልጠናውን እንዲከታተሉ ጠይቀዋል፡፡

በስልጠናው የኢንስቲትዩቱና የቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል ተመራማሪዎች፣ የተቋሙ የስራ ሀላፊዎችና ባለሞያዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *